የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላርን ጎበኙ።

ሐምሌ 5/ 2017 ዓ.ም (ኢሚ) በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢንቨስትመንት የጀመረውና የሶላር ኃይል ማመንጫ የሚያመርተው ቶዮ ሶላር (TOYO SOLAR) ካምፓን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ጎብኝተዋል።

የፀሃይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን የአመራረት ሂደት እና የምርት ጥራት ሚኒስትሩ የተመለከቱ ሲሆን ይህም ሀገራችን ከያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲ ጋር የተናበበ በማድረግ በሀገሪቱ በማደግ ላይ ላለው የኃይል ጥያቄም ምላሽ በመስጠት ሊያግዝ የሚችል መሆኑን በጉብኘቱ ወቅት ተገልጿል ።

በጉብኝቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፣ አቶ ሀሰን መሀመድ እና የሲዳማ ክልል የዘርፋ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post