አምራች ኢንዱስትሪዎች ህልውናቸውን ለማስቀጠል የማምረት አቅማቸውን በቀጣይነት ማሳደግ አለባቸው(አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)
ሀምሌ 8/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚንስትር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በኦሮሚያ ክልል በታጠቅ ኢንዱስትሪ ሰፈር የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ፡፡
አቶ ታረቀኝ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ ሆነው ህልውናቸውን ለማስቀጠል የማምረት አቅማቸውን በቀጣይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሳደግ እንዳለባቸው በጉብኝት መርሀ ግብራቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለማወቅና የሚያስፈልጋቸውን የድጋፍ አይነት በመለየት ወደ ተግባራዊ መፍትሔ ለመስጠት ስለመሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ጉብኝት የተደረገባቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገላቸው ባለው ድጋፍና ክትትል መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን ሚንስትር ደኤታውም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከብድር አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያሉባቸውን ችግሮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታችው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ለመፍታት እየሰራ እንደሆነና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
የተጎበኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ታጠቅ ትራንስፎርመር ፋብሪካ፣ከባድ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ና አድባንቴጅ ኢንዱስትሪያልስ ናቸው ፡፡