ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ለሀገራዊ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው (አቶ መላኩ አለበል )
ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና 2018 ዓ.ም ዕቅድ ውይይት ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት በ2017 በጀት ዓመት ለኢንዱስትሪው እንደ ሃገር ስኬታማ የሆንበት ዓመት ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡
በዚህም በዋናነት መንግስት እየሰራባቸው ያሉ ዘርፎች ኤክስፖርትን ማበረታታት ፤ ገቢ ምርት መተካት፤ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር ፤የማምረት አቅም አጠቃቀምን በማሳደግ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ሃገራዊ ኢኮኖሚዊ አብርክቷቸው ከፍተኛ የሆነበት ዓመት ነው ሲሉ ገልፀዋለ ፡፡
ቀጥለውም በአምራች ኢንዱስትሪዎችን በስፋት በማስተዋወቅ ትስስራቸውን በማጎልበት በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ገፅታን በመገንባት የዕውቀት ሽግግር የልምምድ ልውውጥ በማካሄድ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት ዘርፉን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማሰራጨት የምርቶች ማስታወቂያ ኤግዚቢሽኖችና ኤክስፖዎች በማዘጋጀት ስኬታማ የሆንበት አመት ነው ብለዋል ፡፡
በተቋማት መካከል ያለውን የቅንጅት ችግር የሚፈታ ለማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪው ምቹ መደላድል የሚፈጥር የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በርካታ ስራዎች ሰርቷል ያሉት ሚኒስትሩ ነገር ግን ኢትዮጵያ ልደርስበት ከሚገባት ርቀት አንፃር የእስካሁኑ ስራ ገና ጅምር ስራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል ፡፡
ኢዱስትሪው ሃገራዊ እድገት ለማምጣት የማይተካ ሚና አለው ይህንን ለማሳካት የጥናት እና ምርምር ተቋማትን አቅም በሚገባ በመጠቀም በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን በእውቀት በመደገፍ በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ ስራ እንዲኖር በማድረግ ሃገሪቷ ከኢንዱስትሪው ማግኘት የሚገባትን ገቢ ማግኘት ትችላለች ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በ2018 ዓ.ም እንደ ሃገር ከዘንድሮ በተሻለ ውጤታማ ለመሆን በዚህ ዓመት ያሉንን ጠንካራ ጎኖች በይበልጥ በማጠናከር ደካማ ጎኖችን ደግሞ ማስተካከያ በማድረግ ለተሻለ ስራ መነሳት አለብን ሲሉ ገልፀዋል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት