አካባቢ ተኮር አምራች ኢንዱስትሪዎች በሁሉም ቦታ እንዲስፋፋ እየተሰራ ነው (አቶ ሀሰን መሀመድ)
ሀምሌ 17/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ፍትሃዊ የሆነ የሀብት ክፍፍልን ለመተግበር አካባቢ ተኮር አምራች ኢንዱስትሪዎችን በሁሉም ቦታ ለማስፋፋት መንግስት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ቀደም ሲል አብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ምቹ በሆኑ ጥቂት ቦታዎች መገንባታቸውን ያወሱት አቶ ሀሰን አሁን ግን በሁሉም አካባቢ ያሉትን ፀጋዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በየአካባቢው ካለው ተፈጥሯዊ ፀጋ ጋር አብረው የሚሄዱ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በሁሉም ቦታ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ሚንስትር ደኤታው አምራች ኢንዱስትሪው ለሀገራችን ኢኮኖሚው ያለው ድርሻ ከፍ ማለት እንዳለበት ጠቅሰው ዘርፉ እንዲዘምንና የታለመለትን ግብ እንዲያሳካ በርካታ ተስፋ ሰጭ ተግባራት መከናወናቸውንና በተለይም ሀገሪቱ ካላት ሀብት አንፃር ብዙ ያልተሰራበትን የቆዳ ኢንዱስትሪን ዘርፍ ለማሻሻል መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት