በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የተመራ ልዑክ ቡድን የክረምት የበጎ ፍቃድ ማህበራዊ አገልግሎት ስራዎችን በጎንደር ከተማ እያከናወነ ነው።

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተመራ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ በጎንደር ከተማ የክረምት የበጎ ፍቃድ ማህበራዊ አገልግሎት ስራዎችን በጎንደር ከተማ እያከናወነ ነው።

የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለማስጀመር ጎንደር ከተማ ሲደርሱ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎችና የጎንደር የባህል ቡድን በአፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች የልዑካን ቡድን በጎንደር ከተማ ቆይታቸው የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤት ጥገና፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፣ የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍና የጎደር ከተማ የኮሪደር ስራዎችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post