አረንጓዴ አሻራ ስራ የትውልድን ሕይወት መስመር ማስቀጠል ነው (አቶ መላኩ አለበል)

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጎንደር ከተማ አንገረብ ተፋሰስ አካባቢ አረጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ፡፡

በዚህ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እንደገለፁት ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዓለም በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አካባቢን መልሶ ማልማት ስራዎች መካከል ዋናው ነው ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ስራ የተፈጥሮ ሚዛንን ከመጠበቅ ባለፈ ማህበራዊ ግንኙነትን በማጠናከርና አካላዊና አዕምሯዊ ጤናን በማስተካከል ሚናው ከፍተኛ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ቀጥለውም ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር የአካባቢ ስነምህዳርን በማስተካከል የአካባቢ ጥበቃ ስራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ ገልፀዋል።

ለኑሮ ተስማሚ የሆነው ጎንደር የበለጠ ተስማሚ እና ምቹ እንዲሆን በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ለትውልድ የሚሻገር ስራ እንሰራለን ሲሉ ገለፀዋል።

በዚህ አመት በመትከል ማሰራራት በሚል መሪ ቃል እንደ ሃገር ሰባት ቢሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

መትከል ብቻ ሳይሆን የተከለውን ተንከባክቦ ማሳደግ እና ፍሬማ እንዲሆን መከባከብ የሁሉም ዜጋ ግዴታ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post