ለመጪው ትውልድ የተሻለ ነገር ይገባዋል (አቶ መላኩ አለበል)

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ በጎንደር ከተማ ለሚገኙ 1ሽ 500 ተማሪዎች የመማሪያ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት ሀገር የሚገነባው መጪው ትውልድ ላይ በመስራት ነው።

መጪው ትውልድን ማስተማር ከትውልድ ትውልድ የሚደረገው ቅብብሎሽ የሰመረ ለማድረግ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አይነተኛው መንገድ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ያሰብነውን ብልፅግና እንደ ሀገር ለማምጣት ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመሆን ሰላሙን ማፅናት ይገባዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የፌደራልና የክልል መንግስታት ለከተማዋ ልማት በትኩረት እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ለአካባቢው ሰላም እያበረከቱት ያለው ስራ የሚደነቅ በመሆኑ አመስግነዋል።

ለተማሪዎቹ የተደረገው ድጋፉ ደብተር ፣ ቦርሳ እና እስክርቢቶ ነው።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post