የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጎንደር ከተማ የኮሪደር ስራ እና የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስትን ጎበኙ።

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል የተመራ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ እና የአፄ ፋሲል ቤተ መንግስትን በጎበኙበት ወቅት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው እንደገለፁት ጎንደር ታሪካዊ እና ጥንታዊ ከተማ እንደመሆኗ በስሟ ልክ መድረስ የነበረባት ቦታ ያልደረሰች በመሆኗን ይህንን ቁጭት ለመወጣት የከተማዋን የኮሪደር ልማት ደረጃውን በጠበቀ መንገድ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በኮሪደር ልማት ቀደመው ከጀመሩ ከአዲስ አበባ ከተማ ልምድ በመውሰድ የራሳችንን ዕውቅት እና ክህሎት በመጨመር የከተማው መንገዶች ደረጃውን ጠብቀን እየተሰራን ነው ብለዋል።

የከተማው የውሃ መፈሳሻ ቦዮችም ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በከተማውም የተገነቡ ሲሆን የከተማውም ህንፃዎች ወጥ የሆነ የቀለም ቅብ እንዲኖራቸው በማድረግ ለከተማው ተጨማሪ ገፅታ አላብሰዋል ብለዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው አክለውም ለከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማት ለእኛ ብዙ ነገራችን ነው የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገፅታ መቀየር ብቻ ሳይሆን የስራ ባህላችንን ማሳደግ ያስቻለ ለቱሪስት ፍሰቱ ከፍተኛ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል።

የከተማዋ አጠቃላይ የኮሪደር ስራ በመጪው መሰከረም ይጠናቀቃል ሲሉ ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post