በኢትዮጵያ በአግሮ ኢንዱስትሪ የሚመረቱ ምርቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው ( አቶ ሃሰን መሃመድ)
ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በሶስቱ አግሮ ኢዱስትሪ ፓርኮች ማለትም በቡልቡላ ፣ ይርጋለምና ቡሬ ለሚመሩቱ ሰላሳ አራት ለሚጠጉ የምግብ ምርቶች ደረጃ ለማውጣት የውል ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የግብዓትና መሰረት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሃሰን መሃመድ እና የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ወ/ሮ መሰረት በቀለ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
በፊርማው ስምምነቱ ወቅት አቶ ሃሰን እንደገለፁት የውል ስምምነቱ በጣም አስፈላጊ እና በኢትዮጵያ የሚመረቱ የአግሮ ኢንዱስትሪ ምርቶች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው እንዲሆኑና የግብርና ምርቶችን በብዛት እና በጥራት እሴት ጨምረን በማምርት ወደ የትኛውም የዓለም ክፍል በቀላሉ ተቀባይነት እንዲኖረን እና ተደራሽ እንድንሆን ዓለም አቀፍ ደረጃዎችንና መመዘኛዎችን ጠብቀን ማምርት ዋነኛው እና አይነተኛው መንገድ ነው ብለዋል ፡፡
ወ/ሮ መሰረት በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ማበርከት በሚያስችል ሁኔታ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር አብሮ በመስራት የግብና ምርቶችን እሴት ጨምሮ በጥራት ለማምረት ጊዜ ወስደን እና ተወያይተን በጋራ ለመስራት ተስማምተናል ፡፡ የነዚህ ምርቶች ደረጃ መውጣት ለሌሎች ምርቶችም እንደ መንደርደሪያ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የደረጃዎች ልማት ስምምነቱ በስድስት ወር እንደሚጠናቀቅ እና አጠቃላይ በጀቱም 30 ሺህ ዩሮ እንደሆነ ተገልፃል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት