መንግስት የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት በየጊዜው የአሰራር ማሻሻያዎችን እያደረገ ነው(አቶ ታረቀኝ ቡልልታ)

ሀምሌ 23/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግሮች ለመፍታት በየጊዜው የአሰራር ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ ታረቀኝ ምንም እንኳን በየጊዜው መንግስት የአሰራር ማሻሻያዎችን በማድረግ ምቹ ሁኔታ ቢፈጥርም አምራች ኢንዱስትሪዎች ይህንን መልካም ዕድል ከመጠቀም አኳያ ውስንነት ያለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሚንስትር ደኤታው መንግስት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች ያደረገላቸው ዘርፎች የሚጠበቀውን ያህል ውጤት እንዲያመጡ አምራች ኢንዱስትሪዎች ራሳቸውን ገምግመው ያለባቸውን ድክመት መቅረፍ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

አክለውም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከኤክስፖርት አንፃር ያለባቸውን የገበያ ችግር ለመፍታት አማራጭ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን መፈለግና ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት አሟልተው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካ ገበያን ከመጠቀም አኳያ ሰፊ ስራ መሰራት አለበት ያሉት አቶ ታረቀኝ በቆዳው ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚመለከታቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች ጠንካራ ማህበር በመመስረት ዕሴት መጨመር ላይ ትኩረት አድርገው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም አምራች ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን ሁሉንም ዓይነት ችግር ለመፍታት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የድጋፍና ክትትል ማዕቀፍ እንደሚያዘጋጅ ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post