አምራች ኢንዱስትሪዎች በዘርፉ ለሚስተዋሉ ተግዳሮቶች የመፍትሔ አካል ሊሆኑ ይገባል(አቶ ስለሺ ለማ)

ሀምሌ 23/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ አምራች ኢንዱስትሪዎች በዘርፉ ለሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ከመንግስት ጋር በመቀናጀት የመፍትሔ አካል ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

አቶ ስለሺ ችግሮች ሳይቆዩ እንዲፈቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለይተው ለሚመለከተው ባለድርሻ የማቅረብ ሀላፊነት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በሀገር ደረጃ የተያዘውን የኤክስፖርት ዕቅድ ለማሳካት አምራች ኢንዱስትሪዎች በትኩረት መስራት እንዳለባቸውና በ2018 በጀት ዓመት የሚደረግላቸው ድጋፍም አፈፃፀፀም ተኮር እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ችግሮችን ከስር ከስር ለመፍታት የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች ተከታታነት ያለው ውይይት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post