መንግስት በወሰደው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮች መፈታት ችለዎል

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዶኔዥያ ብሔራዊ የልማት እቅድ ሚኒስትር ራችማት ፓምቡዲ በኢትዮጵያ የኢንዶሚን አምራች የሆነውን ሳሊም ዋዛራን ያህያ ምግብ ኃ. የተ. የግ .ማህ በመገኘት የስራ ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝቱ መንግስት በወሰደው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ድርጅቱን ሲያጋጥሙት የነበሩ ችግሮች ማለትም የውጪ ምንዛሬ እጥረት፣ የኃይል አቅርቦት፣ የኔት ወርክ፣ የገበያ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ጥያቄዎቻቸው መመለሱን የገለጹት በድርጅቱ የሀገር በቀል ባለድርሻ ተወካይ የሆኑት አቶ ሰዒድ ያህያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የስንዴ አቅርቦት፣ ጥራት እና የዋጋ ሁኔታ እንዲሁም ከታክስ ስርዓት ጋር በተያያዘ እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮች ቢቀረፉ የድርጅቱ የማምረት አቅም ላይ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ አስፈላጊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

የኢንዶኔዥያ ብሔራዊ የልማት እቅድ ሚኒስትር ራችማት ፓምቡዲ በበኩላቸው የሁለቱን አገራት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት እንሰራን ሲሉ ተደምጠዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post