ኢትዮጵያዊያን በአረንጓዴ አሻራ በዓለም ላይ ምሳሌ የሚሆን ትልቅ ታሪክ እየሰሩ ነው (አቶ መላኩ አለበል)

ሐምሌ 24 /2017 ዓ.ም(ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ከተጠሪ ተቋማቱ፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በእንጦጦ በመትከል ማንሰራራት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኝ የአረንጋዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል በችግኝ ተከላው ወቅት እንደገለፁት አረንጓዴ አሻራ እንደ ሃገር ያለው ፋይዳ ትልቅ ከመሆኑም በላይ ደን ሕይወት መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ የመንተክለው ችግኝ ነገ ለሃገር ለትውልድ የሚተርፍ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ችግኞችን የምንተክለው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ፣ ግድቦቻችንን ከደለል ለመጠበቅ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎችን ለማግኘት መሆኑንም ገልፀዋል።

ቀጥለውም ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ዛሬ በአንድ ጀንበር እንደ ሃገር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መረሃ ግብር አንድ አካል የሆነ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል ፡፡

በአረንጓዴ አሻራ ተፈጥሮን በመከባከብ በዘላቂነት የተስተካከለ ተፈጥሯዊ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ ከተፈትሮ የሚገኘውን በረከት ለማግኘት እና እንደ ሃገር ያሰብነውን ለኑሮ ተስማሚ የሆነች በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝምና በንግድ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ትክክለኛው መንገድ ችግኝ መትከል፣ መከባከብ እና ማሳደግ ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post