ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለኢንዱስትሪ እና ለቱሪዝም ዕድገት አረንጓዴ አሻራ ፋይዳው ብዙ ነው ። ( አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

ሐምሌ 24 /2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በእንጦጦ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በችግኝ ተከላው ወቅት እንደገለፁት ኢትዮጵያን መልሰን አረንጓዴ እያለበስን በመሆኑ አሁን ላይ ምንጮች እየጎለበቱ ለኑሮ እና ለአካባቢ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠረ በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በየዓመቱ የራሳችንን ስራ እያሻሻልን የሄድንበት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለሌሎች አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን ምሳሌ የሆንበት ነው ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው በመሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

ለመጪው ትውልድ የተሻለ ለኑሮ ተስማሚ እና የበለፀገች ኢትዮጵያን እናወርሳለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post