በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግንዛቤ የተፈጠረባቸው የማምረት አቅም አጠቃቀምና የተኪ ምርት በተሟላ አኳኋን ይተገበራሉ (አቶ መላኩ አለበል)
ሀምሌ 24/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የክልል፣የከተማ አስተዳደርና የተጠሪ ተቋማት የዘርፉ አመራሮች በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና በ2018 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ዙሪያ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው፡፡
የምክክር መድረኩን በንግግር ከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግንዛቤ የተፈጠረባቸው የማምረት አቅም አጠቃቀምና የተኪ ምርት በ2018 በጀት ዓመት በተሟላ አኳኋን ይተገበራሉ ብለዋል፡፡
አቶ መላኩ በ2017 በጀት ዓመት የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተተገበረበትና ከውጭ ምንዛሬ ግኝትና ከብድር አቅርቦት ጋር ተያይዞ የነበሩ ችግሮች የተቀረፉነት በመሆኑ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ምቹ ሁኔታ የተፈጠረበት ዓመት ነበር ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በበጀት ዓመቱ በተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የገበያ ትስስር እንደተፈጠረና ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስሉም እጅግ በጣም ብዙ ውጤታማ ተግባራትን እንደፈፀመ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ገቢ ምርትን በመተካት ረገድ ስትራቴጅ ተቀርፆ ዘላቂ በሆነ መንገድ እየተሰራበት በመሆኑ ከዚህ በፊት ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶች አሁን ላይ አብዛኞቹ ሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ እየተመረቱ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የውይይት መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት