ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚወጣውን ከፍተኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት ለመቀነስ በትኩረት ልንሰራ ይገባል (የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሃመድ)
ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ)ይህ የተገለፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት አመት የዘርፉ አፈፃጽምና በ2018 በጀት የመነሻ እቅድ ዙሪያ ከተጠሪ ቋማቱና ከክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ባካሄደው መድረክ ነው።
በ2017 በጀት አመት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ክፍተት በታየባቸው ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር የግብዓትና መሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሐመድ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባቸዋል ያልዋቸውን ርዕሰ ጉዳዮች አንስተዋል።
ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚወጣው የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት ከፍተኛ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ የተጀመሩ የአማራጭ ሃይል አቅርቦት፣ የአቅም ግንባታ እና የኢነርጂ ኦዲት ስራዎች አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
የግል ዘርፉ ስኬት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት ወሳኝነት አለው ያሉት አቶ ሃሰን ክልሎች የዘርፍ ማህበራትን በማደራጀት ፣የሰለጠነ የሰው ኃይል እና ብቁ አመራር በመፍጠር እና ጥራት ያለው ጊዜውን የጠበቀ እና ታማኝነት ያለው የመረጃ ስርዓት በመዘርጋት እንዲሁም አጠቃላይ የግብዓት አቅርቦትና ግብይት ትስስር ጉዳዮች ላይ አትኩረን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት