የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የላቀ አፈፃጻም ላስመዘገቡ ተጠሪ ተቋማትና የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች እውቅና ሰጠ

ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ) ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2017 በጀት አመት የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች የመደበኛ ስራዎች አፈፃጻምን ከአሰራር ስርዓት አንፃር 14፣ ከቁልፍ ውጤት አመላካቾች አንፃር 12 እና ከኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አንፃር 4 በድምሩ 30 መመዘኛ ነጥቦችን በማዘጋጀት ግምገማ አድርጓል ።

በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረትም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ከፍተኛ አፈፃጻም በማምጣት ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ ኦሮሚያና አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃጻም ያላቸው ክልሎች በመሆን ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ሽልማት ተቀብለዋል።

ከተጠሪ ተቋማትም የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የላቀ አፈፃጻም በማምጣት ተሸላሚ ሆኗል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post