የዘርፉን የላቀ አፈፃፀም አጠናክሮ ለማስቀጠል በየደረጃው የሚገኝ የአመራር ሚና ወሳኝነት አለው ( አቶ መላኩ አለበል)

ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ አፈፃፀም መምጣቱ ተቋሙ ባደረገው የአፈፃጸም ግምገማ ገለፃ ተድርጓል።

ለስኬቶቹ በምክንያትነት ከተጠቀሱት መካከልም ከፌደራል እስከ ክልልና ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት ጋር በዘርፉ እቅድ ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዙ፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ቀጣይነት ባለው መልኩ መቀጠሉ፣ የነበሩ ክፍተቶችን ለመድፈን ቀጣይነትና ዘላቂነት ያለው አካሄድ ተግባራዊ መደረጉ፣ ችግሮችን በእውቀትና በጥናት ለይቶ በዘላቂነት ለመፍታት የተሄደበት ርቀት፣ የተፈጠሩ አደረጃጀቶችና እነሱን ተከትሎ የተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶች እንዲሁም የክትትልና ድጋፍ ስርዓቶች መሻሻል ለስኬቶቹ ምክንያቶች በመሆናቸው አጠናክረን ልንቀጥ ይገባል ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ የፖሊሲና ስትራቴጂ ትግበራን ማጠናከር ፣ የመረጃ ስርዓት ማጠናከር ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስልን በተመለከተ፣ የኢንተርፕራይዝ ቆጠራን በተመለከተ የማምረት አቅም አጠቃቀም ማሳደግ፣ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ከማስፋት፣ ለአነስተኛ መካካለኛ ኢንተርፕራይዞች ልዩ ትኩረት መስጠት፣ ለተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ አጠናቆ ወደ ተግባር ምዕራፍ ማሻገር፣ ለኤክስፖርት እና ተኪ ምርት ልዩ ትኩረት መስጠት እንዲሁም ከኢ- ኮሜርስ ተግባራዊነት ማሳደግ የሚሉት በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫነት የተለዩ ጉዳዮች መሆናቸውንም አቶ መላኩ ጠቅሰዋል።

በዘርፉ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና ለቀጣይ የዘርፉ እቅድ መሳካትም በእቅውቀትና ክህሎት የዳበረ እንዲሁም ቁርጠኛ አመራር ሚና ወሳኝነት አለው ሲሉ ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post