ኢትዮጵያ ከጆርዳን ጋር ያላትን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የማድረስ ጽኑ ፍላጎት አላት (አቶ ሀሰን መሀመድ)

ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በኢትዮጵያ የጆርዳን አምባሳደር ዶ/ር ኢማድ መሳልሜህ በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ::

የጆርዳን እና የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው ያሉት አቶ ሀሰን መሀመድ ሁለቱ ሀገራት የዘላቂ ልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ የጋራ ራዕይ እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡

ሀገራቱ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስራት እንደሚገባቸው የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው የጆርዳን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቱሪዝም እና አገልግሎት ዘርፍ መሰማራት የሚችሉባቸው በርካታ እድሎች እንዳሉ ገልፀዋል፡፡

አቶ ሀሰን አክለውም ጆርዳን በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በፋርማሲዩቲካል እና ሶላር ማምረት ላይ ያላትን ልምድ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የጆርዳን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ስነ-ምህዳር ውስጥ ፈጠራን እና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በመሳተፍ ኢንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በኢትዮጵያ የጆርዳን አምባሳደር ዶ/ር ኢማድ መሳልሜህ በበኩላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ እየተደረገ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባር ለሀገር ዕደገት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ዘርፉን ለማሳደግ ወደ ተግባር በመግባት በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post