የኔዘርላንድ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፤ ግብርና፣ ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ላይ ውጤታማ እና ለሌሎች ሀገሮች ተምሳሌት ናቸው ( አቶ መላኩ አለበል )

ሐምሌ 5/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር የሆኑትን ክብርት ክሪስቲን ፒሪን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ ፡፡

በኢትዮጵያ ስላሉት የኔዘርላንድ ኢንቨስትመንት መንግስት የቅርብ ክትትል ድጋፍ በሚያደርግበት ሁኔታ ላይ እና ተጨማሪ ኢንቨስትመንት መሳብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል ፡፡

በውይይቱ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት የኢትዮጵያ እና የኔዘርላንድ መንግስት ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው ብለዋል፡፡

የኔዘርላንድ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፤ በግብርና እና በቱሪዝም ኢንቨስትመንት ተሰማርተው ለሌሎች ሀገሮች ተምሳሌት የሚሆን ውጤታማ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡

ኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል እና ለእርሻ ምቹ የሆነ መሬት ያላት እንዲሁም በተፈጥሮና በማዕድን የበለፀገች ሃገር ናት ያሉት ሚኒስትሩ አቶ መላኩ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ለሚያደርጉ ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ፣ የታክስ እፎይታ ፣ ከቀረጥ ነፃ ዕድል ፣ ለኢቨሰትመንት የተመቻቸ የአሰራር ሰርዓት መኖሩን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በታዳሽ ሃይል፣ በእርሻ ሜካናይዜሽን ፣በማኒፋክቸሪግ፣ በማዕድን እና በቱሪዝም አብረውን መስራት ለሚፈልጉ ምንግዜም በራችን ክፍት ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም መንግስት ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከሎጀስቲክ፣ ከገበያና ግብዓት ትስስር እንዲሁም ከመሰረተ ልማት እና ከፀጥታ ጋር በተያየዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ክብርት ክሪስቲን ፒሪን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለሆላንድ ትልቅ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን ጠቅሰው በልማት ትብብርም ከአፍሪካ ሀገሮች ከፍተኛውን ድርሻ የምትይዝ ሀገር መሆኑኗን ገልፀዋል ፡፡

በኢትዮጵያ ስላለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ኢንዱስትሪ ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሯ ዘርፉን ለማሳደግ ለሚሰራው ስራ ኔዘርላንድ ሁሌም አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post