ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስኬት የሲቪል ሰርቪሱ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ሪፎርም ወሳኝ ነው ። (አቶ መላኩ አለበል)

ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዘርፉን ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደራዊ ሪፎርሙን በተመለከተ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፣ ከተጠሪ ተቋማቱ፣ ማዕከላትና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በመንግስት ደረጃ ቅድሚ ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ መሆኑን አስታውሰው የዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ድርሻ ለማሻሻል የፖሊሲ ማሻሻያ፣ አዋጆች፣ የማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችና መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ስራ የተገባ መሆኑን በመጥቀስ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ የእድገት ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል ተቋማዊ ሪፎርም ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የተቋማትን የአሰራር ሪፎርም ግብ ለማሳካት የሲቪል ሰርቪሱን ሪፎርም ተግባራዊ መሆን ይጠበቅበታል ያሉት ሚኒስትሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራችንን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት፣ ለዘርፉ እቅድ ስኬትና ለህዝብ አገልግሎት ራሱን የሰጠ አገልጋይ መፍጠር የግድ ይላል፡፡

የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት፣ ወጭን ለመቀነስ፣ አፈፃጸምን የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ፣ ፍትሃዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋ፣ ሁሉን አቀፍ መሻሻል ለማምጣትና የህዝብን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ ለመመለስ የሲቪል ሰርቪሱ ሪፎርም እንደመልካም አጋጣሚ የሚወሰድ ስራ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አክለውም ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጅ መጠቀምና የዘርፉን ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ ተገንዝቦ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ትውልድ የተሻለ አሻራ ለመጣል በትጋት የሚሰራ ተቋማዊ አደረጃጀትና አሰራር መዘርጋት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል ።

በውይይቱ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያለፉት ዓመታት ስኬቶች ማብራሪያ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ የቀረበ ሲሆን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር መኩሪያ ኃይሌ ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደራዊ ሪፎርሙን የተመለከተ ሰነድና ሰፋ ያለ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post