የአምራች ኢንዱስትሪ ሀገራዊ ዕድገት ሚና
• የኢኮኖሚ ዕድገት፡- ማኑፋክቸሪንግ ለአንድ ሀገር አጠቃላይ ሃገራዊ እድገት (GDP) ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያመጣል።
• የሥራ ዕድል ፈጠራ፡- ለብዙ ዜጎች የስራ ዕድሎችን በመፍጠር የሥራ አጥነትን መጠን ከመቀነስ ባለፈ ፍሬያማ ትውልድ ይፈጠር ዘንድ ጉልህ ሚና ይጫወታል ።
• ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማትን ማሳደግ፡- ኢንዱስትሪው በምርምር እና በልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ ፈጠራን ያበረታታል፣ ይህም የቴክኖሎጂ ዕድገትን ያመጣል።
• የወጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደግ፡- ሀገራት ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን እንዲያመርቱ፣ የንግድ ሚዛኖችን እንዲያሻሽሉ እና የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኙ ያስችላቸዋል።
• የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፡- የማኑፋክቸሪንግ ዕድገት ብዙ ጊዜ ወደ ተሻሻሉ መሠረተ ልማቶች ማለትም ትራንስፖርትና መገልገያዎችን ጨምሮ ሌሎች ዘርፎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።
• ክህሎትን ማዳበር፡- የክህሎት ዕድገትን እና የሙያ ስልጠናን ያበረታታል፣ የሰራተኛውን አቅም ያሳድጋል።
• የአቅርቦት ሰንሰለት ዕድገት፡- ማምረት የአቅራቢዎችን እና የአገልግሎት አቅራቢዎችን ግንኙነት እንዲኖር ያግዛል፣ ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎች ዕድገትን ያበረታታል።
• ክልላዊ ልማት፡- በክልሎች እና በከተሞች አካባቢ ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲኖር በማድረግ በጋራ የማደግ የመልማት ዕድል ይፈጥራል ፡፡
• ምርታማነትን መጨመር፡- ሴክተሩ ብዙ ጊዜ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ሂደቶችን በመጠቀም የምርታማነት ማሻሻያዎችን ያደርጋል።
• መረጋጋት፡- ጠንካራ የማኑፋክቸሪንግ መሰረት ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን እንዲኖር ያደርጋል፣ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ከሌሎች ዘርፎች ጋር ሲነፃፀር በኢኮኖሚ ውድቀትን ይቋቋማል።
በአጠቃላይ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚዊ ዕድገት፣ ልማትና ሰላም ወሳኝ ሚና የሚጫወት ቁልፍ ዘርፍ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለዘርፉ እድገት የበኩሉን ድርሻ ቢወጣ መልካም ነው እንላለን።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት