ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ስራዎች እየተሰራ ነው(ዶ/ር ደስታው መኳንንት)
ነሀሴ 7/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የሃይል አጠቃቀም ለማሻሻል የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር ደስታው መኳንንት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በአገራዊ የኢኮኖሚ አድገት ላይ ወሳኝነት እንዳለውና ላለፉት አመታት እያመጣ ያለው ለውጥ አበረታች መሆኑን ገልጸው የዘርፉ ዘላቂ እድገት ያለ ኢነርጂ ሊሳካ አይችልም ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የዘርፉን የኃይል አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ የኃይል አቅርቦት ጎን ለጎን በአምራች ዘርፉ የሚሰተዋሉ የኃይል አጠቃቀም ብክነቶች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የኃይል አጠቃቃም ብክነቶች በኢንዱስትሪዎች ትርፋማነት እንዲሁም እየባከነ ያለውን ኃይል ለሚመለከታቸው እንዳይደርስ በማድረግ ረገድ አሉታዊ ተጽእኖ አለው ያሉት ዶ/ር ደስታው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ኢንዱትሪዎች በቁጠባና በውጤታማነት ኃይልን የሚጠቀሙበትን ስርዓት መዘርጋት በመሆኑ የመግባቢያ ሰነዱ በኃይል አጠቃም ምክንያት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን ተጨማሪ ወጪን በማስወገድ እና የሚመረተው ሃይል በውጤታማነት ለበርካታ ኢንዱስትሪዎች መድረስ እንዲችል ይረዳል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱም አምራች ኢንዱስትሪዎች ኃይል ቆጣቢ የሆነ የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጉ አቅማቸውን የመገንባት እና አስገዳጅ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ እንደሚደረጉ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ እነዚህና መሰል ተግባራትን በማከናውን ለኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መሳካት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚያክናውናቸውን አጋዥ ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት