በኢትዮጵያ ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲመጣ ከዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር በጋራ እንሰራለን (አቶ ሃሰን መሃመድ)

ሐምሌ 8/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ በኢትዮጵያ የስዊዲን ኤምባሲ የንግድ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ም/ዋና ፀኃፊ የሆኑትን ሚስተር ሃምፓስ ሆልመር እና የአውሮፓ ዩኒየን የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑትን ሚስተር አድሪን ካኖ ጉሪሮ በፅፈት ቤታችው ተቀብለው አነጋገሩ ፡፡

የውይይቱ ዋና አላማ ኢትዮጵያን መንግስት የልማት አጀንዳ ለመደገፍ እና ለሚሰሩ ስራዎች የጋራ መግባባት ለመድረስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልፃል ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ እንደገለፁት የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብርት እንዲሁም የሲዊዲን መንግስት ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከማንኛውም ሃገር ጋር በጋራ መግባባት እና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት ላይ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ሁሌም ዝግጁ ናት ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ከልማት አጋሮቻችንን የምናደርገው የጋራ መግባባት የኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ ለሚሰጣቸውን ጉዳዮች ተጨባጭ ስራዎችን በጋራ ለመስራት እንዲስችል እና በሂደቱም ሃገራችንን ኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ እድገት ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

አቶ ሃሰን መሃመድ ምንጊዜም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሁሉም የልማት አጋሮቻችን ጋር በቅርበት ለመስራት ጠንካራ እና ቁርጠኛ መሆናኑን አረጋግጠዋል ፡፡

በኢትዮጵያ የሲዊዲን ኤምባሲ የንግድ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ም/ዋና ፀኃፊ የሆኑትን ሚስተር ሃምፓስ ሆልመር እና የአውሮፓ ዩኒየን የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑትን ክቡር አድሪን ካኖ ጉሪሮ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ትልቅ የኢንቨስትመንት፣ የንግድና የቱሪዝም መዳረሻ ናት ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ፣ የታክስ እፎይታ ከቀረጥ ነፃ ዕድል ፣ ለኢቨስትመንት የተመቻቸ የአሰራር ሰርዓት መኖሩን መገንዘብ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡

በልማት ትብብርም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገሮች ከሲውዲን እና ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛውን ድርሻ የምትይዝ ሃገር መሆኑኗን ገልፀዋል ምንግዜም አውሮፓ እና ሲዊዲን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post