በመነሻ ዕቅዱ ላይ በተቀመጡ ግቦች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱ ተገለጸ።
ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ2018 የመነሻ ዕቅድ ዝግጅት ላይ ከፌደራል የቴክኒክ እና የክልል ክላስተር ኮሚቴ አባላት ጋር እያካሄደ ያለው ውይይት አጠናቋል።
የ2017 በጀት ዓመት የንቅናቄውን አፈፃጸም መሰረት በማድረግ የ2018 በጀት ዓመት የኢንዱስትሪ ካወንስል ዕቅድ፣ የስትራቴጂክ ጉዳዮች እና የንቅናቄ መነሻ ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን የዕቅዱ ዋና ዓላማውም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እድገትና ተወዳዳሪነት ተግዳሮትና ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ዋነኛ መንስኤ በመለየት ስትራቴጂካዊ አካሄድና በቅንጅታዊ አሰራር መፍትሄ በመስጠት የማምረት አቅም አጠቃቀምን ማሻሻል ነው ።
በመነሻ እቅዱ ላይ ስድስቱም ክላስተሮች አስፈላጊውን ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ በማጠቃለያው በንቅናቄው የ2018 መነሻ እቅድ በተቀመጡ 13 ግቦች ላይ የጋራ መግባባት መያዙን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ፅ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር አያና ዘውዴ ገልፀዋል።
ከዝግጀት ምዕራፍ አንፃር የንቅናቄውን ዕቅድ ከዋና ስራዎች ጋር በማሳለጥ እና ለተቀመጡ ተግባራት ግልፅ የሆነ መመዘኛ በማስቀመጥ ረገድ ካለፉት አመታት አንፃር ትልቅ መሻሻሎች ታይቷል ያሉት ዶ/ሩ በቀጣይም የተጠቃለለ እና የተደራጀ ዕቅድ በተዘጋጀው የጊዜ ገደብ ተጠናቆ እንዲቀርብ መልእታቸውን አስተላልፈዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት