የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነት እንዲሁም በጉምሩክ አሰራር ማሻሻያ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
አቶ ሀሰን አክለውም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪ በለያቸው ኢኒሼቲቮች ዙሪያ የማስተግበሪያ የአሰራር ስርዓቶች ዝግጅት በማድረግ የኢንዱስትሪ ማህበረሰብን ተጠቃሚነት እና የህብረተሰብ ተሳትፎ እድገት እና ልማት በሚያረጋግጥ መልኩ ከተለያዩ የልማት አጋሮች በሚገኙ የፋይናንስ የልምድና የቴክኖሎጂ ድጋፎች አቅም በመጠቀም በቀጣይ የግሉ ዘርፍ ችግሮችን በጥናት እየለየ ለመንግስት እያቀረበ የፖሊሲ ችግሮችን የሚፈታበትን መንገድ እየፈጠርን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል።
የጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት (GIZ) ተጠሪ ዳይሬክተር አና ዋልድማን በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖር እና ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚዊ እና ማህበራዊ ለወጥ እንዲመጣ ይህንን የፋይናንስ እና የጉሙሩክ አሰራር ጥናት ማሻሻያ ድጋፍ በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ውይይቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ትልቅ አቅም ይሆናል ሲሉ ተናግረዎል።
በውይይት ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የግሉ ዘርፍ ማህበራት የቦርድ አመራሮች እና ባለሃብቶች፣ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።