የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ስራዎች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ሚናዉ ከፍተኛ ነዉ። (አቶ መላኩ አለበል)

መስከረም 20/2018 ዓ.ም (ኢሚ) የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ (ሪፎርም) አሰራርና ዕቅድ ዝግጅት በተመለከተ ለማሻሻያ (ሪፎርም) ኮሚቴ አባላት ከፍተኛ የዘርፉ አመራሮች በተገኙበት ስልጠና እየሰጠ ነው።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርና የስራ አቅጣጫ የሰጡት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን የሲቪል ሰርቪስ የማሸሻያ (ሪፎርም) ስራ ተግባሪዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው የዘርፉን ፖሊሲዎች በመተግበር እንደ ሀገር ልናመጣ የምናስበውን ለውጥ እውን ለማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታችን መዘመን ቁልፉን ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ቀልጣፋ፣ ተገማችና ተዓማኒነት ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት መሰረቱ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻል (ሪፎርም) በመሆኑ ለሪፎርሙ ተግባራዊነት ለፖሊሲዎቻችን መሻሻልና ተግባራዊነት የሰጠነውን ትኩረት ያህል ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል ።

የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ስራው ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ዕድገትና ሀገራዊ የኢኮኖሚ አበርክቶ ከፍ ማለት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለሪፎርሙ መሳካት ሁሉም ዘርፉ አመራር ከሁሉ በፊት ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል ።

በስልጠናዉ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች ተገኝተዎል።

Share this Post