በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የግል ዘርፍ ማህበራት የማይተካ ሚና አላቸው (አቶ መላኩ አለበል)

መስከረም 23/2018 ዓ.ም (ኢሚ) በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጥልና የግል ዘርፍ ማህበራት በዘርፉ እድገት ላይ የሚያበረክቱትን አስተዋፅኦ ማሳደግ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።

የውይይቱ ዓላማም እንደ ሀገር የተቋቋሙ የግል ዘርፍ ማህበራት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት ወሳኝ በመሆናቸው ያሉበት ነባራዊ ሁኔታ ለመቃኘት፣ ውጤታማነታቸው እና ችግሮቻው ላይ ተወያያይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

በውይይቱ የዘርፍ ማህበራት እንደሀገር የሚወጡ ፖሊሲዎችን በማስተዋቅና በማስተግበር፣ የግል ዘርፉን ተዋንያዎች አቅም በማጎልበት ፣የገበያ ዕድሎችን በማፈላላግና ተጠቃሚነትን በማሳደግ ፣በዘርፍ ደረጃ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችና በመፍታት ፣የምርት ጥራትና ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ረገድ ተልዕኮ እንዳላቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል።

ባለፉት አመታት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ ከወጡ የፖሊስ መርሆዎች መካከል አንዱ የሰው ሃይል ልማትና አስተዳደር አንዱ እንደሆነ የገለፁት አቶ መላኩ የግል ዘርፍ ማህበራት በተለይም መንግስት መሸፈን የማይችላቸውን ስራዎች በመሸፈን ረገድ ሚናቸው የማይትካ ነው ሲሉ አክለዋል።

ላለፉት አመታት ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያሰችል የፖሊሲ ማሻሻያና ስትራቴጂዎች መዘጋጀታቸውን፣የዘርፉን እንቅስቀሴ በቅርበት የሚከታተልና ቅንጅታዊ አሰራሮችን የሚያጠናክር የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል መቋቋሙን፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተግባራዊ መደረጉ እና የዘርፉን የመሰረተ ልማት ችግሮች ለመፍታት በርካታ ስራዎችን መሰራቱን የገለፁት ሚኒስትሩ በዚህም የማምረት አቅም አጠቃቀም ፣የገቢ ምርት መጠን እያደገ መምጣቱ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ከፍ እያለ መምጣቱን በመግለጽ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልም የግል ማህበራት መጠናከር፣ በተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች የመንሳቀስና የመስራት ጉዳይ እጅግ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

Share this Post