ሀገራችንን የብልፅግና እና የአፍሪካ የእድገት ተምሳሌት ለማድረግ በጋራ ልንሰራ ይገባል ( አቶ ሐሰን ሙሐመድ)
መስከረም 24/2018 ዓ.ም (ኢሚ) የዘርፍ ማህበራትን እንዴት እናጠናክር ከመንግስትና ከግል ዘርፉ ምን ይጠበቃል የሚለውን ለመመክር በተዘጋጀው መድረክ ላይ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉና ለዘርፍ ማህበራት ትልቅ ትኩረት መስጠቱን ለዚህም ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዘርፍ ማህበራትን የማደራጀትና የመደገፍ ስልጣን እንዳለው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሃመድ ገልፀዋል ።
የዘርፍ ማህበራት መደራጀት በሀገራዊ የኢኮኖሚና በዘርፉ እድገትና ተወዳዳሪነት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የገለፁት አቶ ሃሰን እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከመቸውም ጊዜ በላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ወደ ራስ በመውሰድ በባለቤትንት ስሜት መፍታት ይገባል ሲሉ አክለዋል።
በቀጣይም የዘርፍ ማህበራት በሀገር እና በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገት ላይ ካላቸው ሚና አንፃር የማጠናከር፣ ለአባላቶች ጥብቅና በመቆም የተቀላጠፈ ድጋፍና አገልግሎት የመስጠት፣የሀገር ውስጥ ምርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የመስራት ፣ የዘርፍ ማህበራት የፊትና የኋልዮሽ ግንኙነት ማጠናከር ከግሉ ዘርፍ ይጠበቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሲደረጉ የነበሩ የድጋፍና ክትትል እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ሁላችንም በየተሰማራንበት ዘርፍ ለሀገራችን ብልፅግናና የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ጉዞ በጋራ ተግተን መስራት ይጠበቅብናል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።