ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረትና ድጋፍ በመስጠት በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን ወደ ዉጤት ለመቀየር እንሰራለን። /የጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፕሬዘዳንት አለሚቱ ኡመድ/
ጥቅምት 7/2018ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የሚገኙ የአምራች ኢንዱስትሪ ፀጋዎችን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በመጠቀም ወደ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል ዉይይት ከክልሉ ፕሬዝዳንት አለሚቱ ኡመድ ጋር ዉይይት አደረጉ።
በዉይይቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የክልሉ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ትኩረትና ድጋፍ በመስጠት በክልሉ የሚገኙ ፀጋዎችን ወደ ዉጤት ለመቀየር እንደሚሰሩም የጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ፕሬዘዳንት አለሚቱ ኡመድ ገልጸዋል ።
አያይዘዉም በክልላቸዉ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ዉጤታማ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የቢሮ አደረጃጀቶችን እና አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግቹ መሆናቸዉንም አንስተዋል ።
በመጨረሻም ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶች በክልሉ መኖራቸዉን ገልጸዉ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ወደ ጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመምጣት መዋለ ንዎያቸዉን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።