ለባለሙያዎቻችን የክህሎት ልህቀትና የቴክኖሎጅ ሽግግር የጃይካ አስተዋጽኦ የጎላ ነው(አቶ መላኩ አለበል)

ጥቅምት13/2018 ዓ.ም(ኢ.ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል አዲሱን የጃይካ (JICA) አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ተወካይ ሚስተር ያኩሽ ሂሮዩኪ(YAkushi Hiroyuki)በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ተወያዩ ፡፡

አቶ መላኩ የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የሚሰጠው የክህሎት ስልጠና ለዘርፉ የቴክኖሎጅ ሽግግር የላቀ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የኢትዮጵያ ስኬት ለሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ስኬት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከጃይካ ጋር ቀደም ሲል የጀመረውን ቅንጅት በማጠናከር በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሚስተር ያኩሽ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ባዩት የዕድገት ለውጥ መደሰታቸውንና በቆይታቸውም ጥሩ የስራ ጊዜ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡

Share this Post