የአምራች ኢንዱስትሪውን አፈፃፀም ከፍ ለማድረግ መንግስት ልዩ ትኩረት ስጥቶ እየሰራ ይገኛል (አቶ መላኩ አለበል )
ህዳር 18/2018 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከቆዳና ሌጦ ሰብሳቢዎች፣ ከቆዳን በግብዓትነት ከሚጠቀሙ የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች ኢንዱስትሪ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅርቦት እና ጥራት ላይ ያተኮረ ዉይይት አካሄደ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በውይይቱ ላይ እንደገለፁት አምራች አንዱስትሪዎቻችን የማምረት አቅም አጠቃቀማቸው 65 በመቶ በላይ እንደደረሰ ጠቅሰዋል፡፡
የቆዳ ኢንዱስትሪዉ የዘንድሮ አፈፃፀም ዕድገት ይታይበታል ያሉት ሚኒስትሩ እድገቱ በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ጠቅሰዉ የሚሰበሰበዉም ቆዳ ጥራት የሌለው በመሆኑ የቆዳ ዘርፉ የሚጠበቀዉን ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ፋዳ እንዲያስመዘግብ በዋናነት የአቅርቦት ሰንሰለቱ መፈተሽ እንዳለበት ገልፀዋል።
በዘርፉ የሚስተዋለዉን ችግር ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የምናደርጋቸው ውይይቶች አስፈላጊ ናቸው ብለዋል።
መንግስት የቆዳውንም ሆነ ሌሎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ችግሮች በመለየት የሚፈታ የአምራች አንዱስትሪ ካውንስል አቋቁሞ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
በውይይቱ ላይ በቆዳ ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ቆዳ ሰብሳቢዎች እና ባለድረሻ አካላት ተሳትፈዋል።