የገብያ ትስስር ለመፍጠር እና ምርታማነትን ለመጨመር የኢንዱስትሪዎች የመስክ ጉብኝት አስፈላጊ ነዉ
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም (ኢሚ) የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና የኢንዱስትሪ ባለሀብቶች የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝን የሥራ እንቅስቃሴ እየተመለከቱ ነው።
በጉብኝቱ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በአማራ ክልል በሚገኙ የአምራቹ ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል የገበያ ትስስር አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።
የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ ራሱን ችሎ ማሽን ማምረት የሚችል እና ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች መለዋወጫዎችን ማምረት የሚችልበት የቴክኖሎጅ፣ የሰው ኃይል እና የግብዓት አቅም ያለው ነው ብለዋል።
ፍብሪካዉ በሙሉ አቅሙ እንዳያመርት ካደረገው ችግር አንዱ የገበያ ትስስር እንደሆነ ሚኒስትሩ አንስተዉ ችግሩን ለመቅረፍ በሀገሪቱ ያሉ የስኳር እና የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በርካታ መለዋወጫዎችን እና ማሽኖችን ስለሚጠቀሙ ከእነሱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመስክ ምልከታ እንደሆነም ገልጸዋል።
በተለይ የጉብኝቱ ዋና አለማ ፍብሪካዎቹ ከሀገር ውጭ የሚያስመጧቸዉን መለዋወጫዎች እና ማሽኖችን ከሀገር ውስጥ መግዛት እንዲችሉ ፍብሪካዉ ያለውን አቅም እንዲያውቁ እና እንዲመለከቱ በማድረግ በሁለቱም መካከል የገብያ ትስስር መፍጠር እና ምርታማነትን መጨመር ላይ ያተኮረ ነዉ ሲሉ አቶ መላኩ ገልጸዋል።
በጉብኝቱ እየተሳተፋ ያሉ የስኳር ፋብሪካ እና የሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ ሥራስኪያጆች እንዲህ አይነት አቅም ያለው ፋብሪካ መኖሩን መረጃው እንዳልነበራቸውም ጠቅሰዋል።