የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ሁጃን የኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ዞን የመስክ ምልከታ አካሄዱ

ጥር 7/2018 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ሁጃን የኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ዞን የመስክ ምልከታ አካሄዱ።

በመስክ ምልከታው ወቅትየኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት የኢንዱስትሪ ጉብኝቱ ዋናው አላማ ሁጃን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ እና መንግስት በቀጣይ ኢንዱስትሪውን በሙሉ አቅሙ ምርታማ እንዲሆንና ለሃገር ያለው ኢኮኖሚዊ አብርክቶ ከፍ ለማድረግ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

መንግስት የፖሊሲ ለውጥ፣ የስትራቴጂ እና የተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር የሚያጠናክሩ የማሻሻያ ስራዎችን በመስራት  በማሻሻያዎቹ በመታገዝ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለመጨመርና የአምራች ዘርፉን እድገት በቀጣይነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።  ቀጥለውም ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ማደግ እና መስፋት የሚረጋገጠው በኤክስፖርት አፈፃፀማችን ውጤት ነው።

በመሆኑም በ2030 ዓ.ም ባስቀመጥ ነው ራዕይ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋ እና ተደራሽ ብቃት ያለውና የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ቨርችዋል የአመራረት ስርዓት እንዲከተሉ ለማድረግ ነው ሲሉ ገልፀዋል።  በቀጣይ በመስክ ምልከታው በወሰድነው መረጃ መሰረት እንደ መንግስት ድጋፍ እና ክትትላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ሁጃን የኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ዞን ምክትል ፕሬዝደንት አምባሳደር ተፈሪ መለስ እንደገለፁት ከአሁን ቀደም ጫማ እና ሶል ነው የምናመርተው ካለፈው ስድስት ወር ወዲህ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ ጎበዝ የሚባል ሶላር ሴል የምናመርት ሲሆን በዓመት ሁለት መቶ ሚሊየን ዶላር ኤክስፖርት እናደርጋለን ሲሉ ገልፀዋል።  በቀጣይ የአልሙኒየም እና የሪሳይክሊንግ ፋብሪካ ለመገንባት አስፈላጊው ጥናት እና ዝግጅት ተጠናቋል ሲሉ ገልፀዋል።

መንግስት ለሚያደርግልን የቅርብ ድጋፍ እና ክትትል አመስግነዋል ።

Share this Post