ምግብን በአስፈላጊ ማዕድናት ማበልጸግ የመንግስት ፖሊሲዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል(አቶ ታረቀኝ ቡልልታ)

ምግብን በአስፈላጊ ማዕድናት ማበልጸግ የመንግስት ፖሊሲዎች ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የእድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ ገለጹ፡፡

ጨውን በአዮዲንና በፎሊክ አሲድ ማበልጸግ ያስቻለው የምርምር ውጤትን የማስተዋወቂያ መርሀግብርን የተሳተፉት አቶ ታረቀኝ ዜጎች በሀገሪቱ የሚወጡ የመንግስት ፖሊሲዎችን በመተግበር እንደ ዜጋ ማበርከት ያለባቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ጤንነታቸው በአስፈላጊ ማማዕድናት በበለፀጉ ምግቦች መጠበቅ አለበት ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ሚንስትር ዴኤታው መንግስት ቀደም ሲል ጨውን በአዮዲን የማበልጸግ ተግባር ሲያከናውን ቢቆይም አዲሱ የምርምር ውጤት የፎሊክ አሲድን ስለሚጨምር ዜጎች በበለጸገ ምግብ እጥረት ጤናቸው እንዳይታወክ የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ምርቱ በስፋት ተመርቶ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን እስካሁን የነበሩ የቅንጅት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Share this Post