እንደ ሀገር ያለንን የኢንዱስትሪ ፀጋዎች በመለየት እና ወደ ተግባር በማስገባት የዘርፉን ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል (አቶ ሀሰን መሀመድ)
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደቡብ ኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል።
ከግብዓት ጀምሮ(ከጉሎ እርሻ እስከ የሐር ጥጥ ልብስ ምርት) የሚያመርት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በአግሮ ኢንዱስትሪ ላይ የተሰማራ ፍብሪካም ተገብኝቷል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በጉብኝቱ ላይ በሐር ጥጥ ልብስ ምርት ላይ በተሰማራዉ ፍብሪካ እጅግ አበረታች ስራ እየሰራ መሆኑን አንስተዉ እንደ ሀገር ያለንን የኢንዱስትሪ ፀጋዎች በመለየት እና ወደ ተግባር በማስገባት የዘርፉን ቀጣይነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
ሚኒስትር ዴኤታዉ አክለዉም እንደ ሀገር የተጀመረዉን የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ተስፍ ሰጪ መሆኑን ተናግረዉ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የኢንዱስትሪዉን ዕድገት ማፋጠን እንደሚቻልም አንስተዋል።
የተጎበኙት ኢንዱስትሪዎች ሀገር ዉስጥ ምርትን በጥራትና ተወዳዳሪ አድርጎ በመስራት ለዉጪ ጎብኝዎች በማቅረብ ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር እና አማካሪ ዳይሬክተር አቶ ገለቱ ገነም ገልፀዋል ።
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በአርባ ምንጭ ከተማ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የግምገማ መድረክ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።