አፍሪካ ወሳኝ በሆነ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች(አቶ መላኩ አለበል)
የካቲት 6/2018(ኢ.ሚ) ሰፊ የህዝብ ቁጥር አና መጠነ ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት የታደለችው አህጉራችን አፍሪካ ወሳኝ በሆነ የኢንዱስተሪ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል ገልፀዋል ፡፡
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሰደር ጃን ፌንግን ጨምሮ ፕሮፌሰር ጀፍሪ ሳችስ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት እና ሌሎችም የአፍሪካ የንግድ መሪዎች የተሳተፉበት ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዥሪ ሆቴል እየተካሄደ ነው፡፡
የአፍሪካ የግሉ ሴክተር የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ እጣ ፋንታ በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ያሉት አቶ መላኩ አለበል በእለቱ እየተካሄደ ያለዉ ውይይት የሚጀመርበት ብቻ ሳይሆን ለተግባር እንቅስቃሴ የምንጀመርበት ነው ብለዋል፡፡
ወሳኝ በሆነ የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ወቅት ላይ የምትገኘው አህጉራችን አፍሪካ 20 በመቶው የሚሆንዉን የአለም ህዝብ የሚወክል እና ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት ያላት ቢሆንም እስካሁን ከአለም ማኑፋክቸሪንግ እሴት ከ1.5 እስከ 2 በመቶው ድርሻ ብቻ የምትይዝ ሲሆን የአፍሪካ የእርስበርስ ጠቅላላ የንግድ ልውውጥም ከ15 እስከ 16 በመቶው አይበልጥም ብለዋል፡፡ እነዚህ አሃዞች የሚመላክቱት ስታስቲከሰ ብቻ ሳይሆን የተግባርም ጭምር ነው ብለዋል፡፡
ኢንዱስተራላይዛሽን በታሪክ ቀጣይነት ያለው እድገት መዋቅራዊ ለውጥ እና የስራ እድል ፈጠራ ሞተር ነው ያሉት ሚኒስትሩ የምስራቅ ኤስያ ተሞክሮ እንደሚያሳየው በኤክስፖርት የሚመራ ኢንዱስትሪያላይዜሽን በቻይና ብቻ 800 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ከድህነት አውጥቷል ብለዋል፡፡
ከፊታችን ያለዉ ጥያቄ አፍሪካ በኢንዱስትሪ ማደግ አለባት ወይ የሚለው ሳይሆን ጥያቄው የወጣቶቻችን ፍላጎት ለማሟላት እና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ከአለም ኢኮኖሚ ጋር ለመወዳደር በሚያስችል ፍጥነት እየሄድን ነው ወይ የሚለው ነው፡፡
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተሩ መሪነት የሃገሪቱ የብሄራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ሁለት የአስር አመት የልማት እቅድ በአንድ መሰረታዊ አቅድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን እሱም የግሉን ሴክተር ለሃገራችን ኢኮኖሚ ዘላቂነት ያለው የእድገት ሞተር በመሆኑ ከዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣትም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን መተግበር፣ የፋይናንስ ስርዓታችን ላይ መስራት፣ ሎጅስቲክስን ማሳደግ እና ተቋማትን በማጠናከር ግልጽ እና ሊገመት የሚችል የኢንቨስትመንት አካባቢ ለመፍጠር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
የአፍሪካ የንግድ መሪዎች ቡድን ውይይት መድረክ ለዘርፉ እድገት ከአስፈላጊም በላይ ነው ያሉት አቶ መላኩ የአፍሪካ የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰነው በመግለጫ ብቻ ሣይሆን በተገነቡ ፋብሪካዎች ፡በቴክኖሎጂ ሽግግር በሚፈጠሩ የ፣እሴት ሰንሰለቶች ጥራት እና ብዛት ባላቸው የስራ እድል ፈጠራዎች ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም አንድ ላይ በመሆን በንጹህ ኢነርጂ የሚንቀሳቀሱ እንዱሰትሪዎችን እንገንባ አፍሪካን በጋራ በኢንዱስትሪ እናሳድግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡