ሀገራችን ለኢንዱስትሪ ምቹ እና ሰፊ የቆዳ ስፋትና ብዛት ያለው የሰው ሃብት ያላት ሃገር ናት /አቶ መላኩ አለበል/

መጋቢት 24/2018 የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መለኩ አለበል በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት ሰም ፋብሪዝ ጋር በኢትዮጵያ እና በጣሊያን የሁለትዮሽ የትብብር ማዕቀፍ በተመለከተ ውይይት

አካሂደዋል፡፡

አቶ መላኩ አለበል የጣሊያኑን አምባሳደር ሰም ፋብሪዝን ጋር በጽ/ቤታቸዉ በትኩረት ከተወያዩባቸዉ መካከል የ2026-2028 ጣሊያን ለኢትዮጵያ ያደረገችዉን የ250 ሚሊዮን ዩሮ የሁለትዮሽ ትብብር ማዕቀፍ ቃል መግባትን አስመልክቶ ጣሊያን ማቲ በተሰኘው አቅዷ በኢትዮጵያ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በግብርና፣ በኢትዮያ ታምርት ንቅናቄ እና የማምረት አቅም አጠቃቀሙ ወደ 66.3 ፐርሰንት ያደገዉን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጣሊያን በቴክኖሎጂ እንዴት ማገዝ እንዳለባት ይገኙበታል ፡፡

ቅድሚያ የሚሰጣቸው የማኑፋክቸሪንግ ንዑስ ዘርፎች ላይ ጣሊያን የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስፋት እና እሴት በመጨመር ምርትን ወደ ውጭ በመላክ ላይ እና ለሃገር ዉስጥ አነስተኛ ና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የጣሊያን ኢንዱስትሪያል መሽኖችንና የመለዋወጫ እቃዎችን ድጋፍ ማጠናከር እንዲሁም የሰው ሃይል ልማትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ሃገር አምራቾች ላይ ያለዉን ተጽዕኖ ምን እንደሚመስል ተወያይተዋል፡፡

ከሌሎች የአለምና የአውሮፖ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ የሰው ኃይልና የኤሌክትሪክ የክፍያ ዝቅተኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስትመንት ማድረግ አዋጭ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ሀገራችን ምንም እንኳ ለኢንዱስትሪ ምቹ እና ሰፊ የቆዳ ስፋትና ብዛት ያለው የሰው ሃብት ያላት ሃገር ብትሆንም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ አሁንም የተማረ የሰው ሃይል እጥረት ስላለ ጣለያን በዘርፉ የምታደረገው ድጋፍ ባስፈላጊው ጊዜ የተገኘ እና ሁለቱን ሀገራት እንደ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር የሆኑት ሰም ፋብሪዝ በበኩላቸው ሀገራቸው እያደገ የመጣውን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።

Share this Post