ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጥበቃና የኢኮኖሚ ዕድገት እጅና ጓንት መሆን እንዳለባቸው አጥብቃ ታምናለች (አቶ ሀሰን መሐመድ)
ግንቦት 7/2018 ዓ.ም(ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በጀርመን መንግስት የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዳይሬክተር ጀነራልና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የተመራ ልኡክ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
ውይይቱን የመሩት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጥበቃና የኢኮኖሚ ዕድገት እጅና ጓንት መሆን እንዳለባቸው ታምናለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አቶ ሀሰን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያላይዜሽን የካርበን ልቀትን በሚያባብስ መልኩ ሳይሆን ከካርበን ልቀት ነጻ በሆነ አመራረት፣ በታዳሽ ሀይል ና በኡደታዊ ኢኮኖሚ ና ቀጣይነት ባለው የዕሴት ሰንሰለትን ትኩረት አድርጎ እንዲመሰረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢያ አህመድ አነሳሽነት መሰረት ሀገሪቱ ጉልህ የሆነ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ የልማት ማዕቀፍ ማዘጋጀቷን የጠቀሱት ሚንስትር ዴኤታው ቀጣይነት ያለው የአየር ንብረት ጥበቃ ስራዎችን ለማሳለጥ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል፡፡
አክለውም ከአየር ንብረት ብክለት የጸዳ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ዕውን ለማድረግ ታዳሽ ሀይልን የማስፋፋት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ምቹ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እየተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም መንግስታቸው ከጀርምን መንግስት ጋር በታዳሻ ሀይል ልማት፣በአካባቢ ጥበቃ ፣በአቅም ግንባታና ቀጣይነት ባላቸው የልማት ንቅናቄዎች ዙሪያ አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡
የጀርምን መንግስት የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዳይሬክተር ጀነራል ክብርት ሚስ ብርጊት ኦሪ(Mrs Birgitt Ory) በበኩላቸው በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የኢትዮጵያ ስኬት የሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ስኬት ማለት መሆኑን ጠቅሰው መንግስታቸው አብሮ ለመስራት እጅግ በጣም ደስተኛ መሆኑን