የግሉ ዘርፍ ጥንካሬ የሚለካው በአደረጃጀቱ ነው (አቶ መላኩ አለበል)
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዘጋጅነት ለዘርፉ እድገት የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ሚና ምን መሆን እንዳለበት፤ከዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች የሚጠበቁ ተግባራት፤የማህበራት ምክር ቤቶች አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በውይይቱ ወቅት እንዳብራሩት እንደ ሃገር በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የመንፍልገውን ውጤት ለማስመዝገብ የምንችለው ዘርፉን በሚመለከቱ በእያንዳንዱ ሂደቶች ላይ የግል ዘረፉን በማሳተፍ እና በማጠናክር በመሆኑ ከፌደራል እስከ ታችኛው መዋቅር ያለው የዘርፍ ማህበሩ በጠንካራ ጽ/ቤት እና ለዘርፉ በተዘጋጀ እውቀትና ፤ ክህሎት ባለው እና የኢንዱስትሪ ባህልን በተላበሰ የሰው ሃይል መደራጀት መቻል ሲችል ነው ብለዋል፡፡
የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰን ከውጭ አቻ ማህበራት ጋርም ትስስር ፈጥሮ መስራት እንደሚገባው ገልጸው ኢንዱስትሪዎቻቹህ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ባደረጋቹሁት መጠን በሃገራቹህ ሰለምና ልማት ለማስፈን የራሳቹሁን አሻራ አሰቀምጣቹህ አያለፋቹህ እንደሆነ በመገንዘብ በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የብቃት እና ፈቃድ አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ በሆኑት ወ/ሮካሳዬ ዋሴ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት አመሰራረት እና ዘርፉ አሁን ያለበት ቁመናን የሚመለከት ጹሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በመጨረሻም የቦርድ አመራሮቹ ማኅበራቱ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የአባላትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ችግሮች በመለየት የአጭር የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን በማውጣትና ዘርፉን በማጠናከር ለቀጣይ ስኬቶች እንደሚሰሩ ገልጸዋል።