ኩባንያው ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ የእውቀት ሽግግርን በማምጣት የሄደበት ርቀት የሚበረታታ ነው / አቶ መላኩ አለበል/

ሰኔ 24/2018 ዓ.ም. (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች መገጣጠሚያና ሽያጭ ላይ በተሰማራው ሚጂ ሞተርስ (MJ MOTOR) ተገኝተው የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማም ለአምራች ኢንዱስትሪዎችን የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እያጋጠማቸው ያሉ ትግዳሮቶችን በቅንጅት መፍታት እና የማምረት አቅማቸውን ማሳዳግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በስራ ጉብኝቱ የመስሪያ ቦታ፣ የደረጃዎች (standard) እና የሃይል መቆራረጥ ተግዳሮቶች እያጋጠሙ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ለመፍታትም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቅንጅት እንደሚሰራ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ የእውቀት ሽግግር በማምጣት በርካታ ስራዎችን በኢትዮጵውያን እንዲሰሩ በማድረግ ረገድ የሄደበት ርቀት የሚበረታታ ነው ያሉት አቶ መላኩ በቀጣይም ኩባንያው በተለይም ለሚያመርታቸው ምርቶች በግብዓትነት የሚጠቀማቸውን በሀገር ውስጥ በሚያመርትበትን አግባብ እና የገበያ መዳረሻዎች ማስፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንሚገባው ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠም እና ሽያጭ ላይ የተሰማራ ሲሆን በዚህም ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የስቴት ምጣኔ ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው፣ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር እና የእውቀት ሽግግርን በማምጣትም እንዲሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ለማምጣት የታቀዱ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በሚደረገው እንቅስቀሴ ከፍተኛ ሚናውአ እያበረከተ እንደሆነም በጉብኝቱ ተገልጿል፡፡

Share this Post