የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የአውሮፓ ህብረት የቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

ጥር 23/2015ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢፌዲሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአውሮፓ አባል ሀገራት ባለሀብቶችን ጉዳይ በተመለከተ በጋራ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሃመድ የኢትዮጵያ መንግስት ኢኮኖሚውን ለማሻሻልና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የ10 ዓመት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ አዘጋጅቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጅዎችን በምትቀርጽበት ወቅትና መሰል የቢዝነስ ስራዎችን በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ድጋፋ የነበረው መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ተቀዳሚና ተመራጭ የቢዝነስ መዳረሻ ለማድረግ ከህብረቱ ጋር በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ የግብዓት፣የውጭ ምንዛሬ፣የገበያ ትስስር፣የመሰረተ ልማትና የመሬት አቅርቦትና መሰል ችግርችን በተቀናጀና በተናበበ መንገድ በመፍታት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ አበርክቶ ማሳደግ ያለመ መሆኑን ተናግረው ከቢዝነስ ፎረሙ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ህብረት የቢዝነስ ፎረም በኢትዮጵያ አምባሳደር ሮላንድ ኮቤ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመደገፍና አምራች ኢንዱስተሪውን ለማሻሻል በርካታ ምርቶች ያለምንም ቀረጥ(0 tarif)በሁሉም አባል ሀገራት እንዲላኩ በማድረግ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንድታገኝ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

በመድረኩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ መልካም እድሎች፣ ችግሮችና የፖሊሲ የመፍትሔ አማራጭ ሀሳቦችን የያዘ ሰነድ ቀርቦ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

#ኢትዮጵያ ታምርት

Share this Post