የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን የግብአት አቅርቦት ችግር መቅረፍ ያስፈልጋል ተባለ ።(አቶ ሀሰን መሀመድ )

ህዳር 07/2016 ዓ.ም(ኢሚ) በአኩሪ አተር አልሚ አርሶ አደሮችና እና የምግብ ዘይት አምራቾች መካከል ዘላቂ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በተዘጋጀው መድረክ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ እንደገለፁት የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን የግብአት አቅርቦት ችግር በመቅረፍ ከውጭ የሚገባውን ዘይት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት የውጪ ምንዛሬ ማዳን ይገባል።

በዘርፉ የሚፈጠረውን የስራ ዕድል፣ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአኮኖሚ ዕድገት ለማምጣታት ውጤታማ የሚያደርጉ ምርቶችን ለይቶ በትኩረት መስራት አስፈላጊ ነው ያሉት ሚንስትር ድኤታው የተኪ ምርት ስትራቴጅ በማዘጋጀት የንግድ ሚዛን አለመጣጣምን ለማሻሻል፣ ዕሴት ያልተጨመረበት የወጪ ምርቶች እሴት በመጨመር ለመላክ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይም ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በዘርፋ እያጋጠመ ያለዉን የማስፈፀም አቅም ውስንነት በመቅረፍ አቅምን አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል ከኢንዱስትሪ ፖሊሲዉ የተቀዱ ስትራቴጂዎችን በመቅረፅ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመዋል ።

የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን የግብዓት እጥረት በዘላቂነት መፍታት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሀሰን መሀመድ የቅባት እህሎችና የአኩሪ አተር አምራች አርሶ አደሮች ማህበራትና የዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል ዘላቂና ተመጋጋቢ የሆነ የገበያ ትስስር መፍጠርና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካላት የእለትከእለት ተግባር መሆን እንደለበት ገልፀዋል ።

Share this Post