የአድዋ የብዝሃ ማንነታችን መሰረት ነው (ክቡር አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች 128ኛውን የአድዋ ድል በዓል አከበሩ

የእድገትና ተወዳዳሪነት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ክብረ በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት አድዋ ቅድመ አያቶቻችን ያወረሱን የብዝሃ ማንነታችን መሰረት የሆነ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነፃነት በዓል ነው፡፡

ሌሎች ሀገራት የነፃነት ቀንን ሲያከብሩ እኛ የምናከብረው የድል በዓል በመሆኑ አብዛኞቻችን አድዋ ያጎናፀፈንን ዘርፈ ብዙ ማንነት በቅጡ የተረዳን አይደለንም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ስለ አድዋ ነፃነት ለመረዳት በቅኝ ግዛት የተያዙ ሀገራት ዜጎች ላይ የደረሰውን የማንነት ወረራና ለምዕራባውያን የሚሰጡትን ያልተገባ ክብር ማየት በቂ ነው ብለዋል፡፡

አድዋ ያጎናፀፈንን ድል በየተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ስኬታማ በመሆን የራሳችንን ድል እንደ ቅድመ አያቶቻችን ልናስመዘግብ ይገባል፡፡

እንኳን የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነፃነት ቀን ለሆነው 128 ኛው የአድዋ ድል ቀን አደረሳችሁ!

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post