ሴቶች በሁሉም ዘርፍ የሚገጥሟቸውን ችግሮችና መሰናክሎች በማለፍ የራሳቸውን አቅም ማብቃት እንዲችሉ ያስፈልጋል

አዲስ አበባ የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ኢሚ) በኢትዮጵያ ለ48ተኛ ጊዜ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ "ሴቶችን እናብቃ፣ ልማት እና ሰላምን እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ያለውን ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን (ማርች8) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሌቤር ኦርጋኔዝሽን ጋር በመተባበር እያከበረ ነው ።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዉስጥ ሴቶች ከከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤትነት እስከ ሥራ ዕድል ተጠቃሚነት በስፋት እንደሚሳተፉ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የግብዓትና መሰረተ ልማት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ገልፀዋል ።

ሴቶች በሁሉም ዘርፍ የሚገጥሟቸውን ችግሮችና መሰናክሎች በማለፍ የራሳቸውን አቅም በማብቃት ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ለአገር ልማትና ሠላም ያላቸውን አስተዋጽኦ ይበልጥ ማጠናክር ያስፈልጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልፅግና እዉን እንዲሆን ትልቁን ተፅዕኖ የሚያደርጉት ግማሹን የማህበረሰብ ክፍል የሚወክሉት ሴቶች ናቸው ያሉት አቶ ዳንኤል በማህበራዊ፣ በኢካኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፉ ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የወንዶችን አጋርነት ይዞ ራሳቸውን የሚያበቃ ተግባር መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

ሴቶችን ሁለንተናዊ ሀገራዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ለፋይናንስ፣ ለመረጃ ለዲጂታል ቴክኖሎጂዎች፣ ለመሥሪያና የመሸጫ ቦታዎች ለተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ተደራሽ የሚያደርጓቸዉን የሥራ አካባቢ ምህዳሮችና አስቻይ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች የሚቀረፅበትና የሚተገበሩበት የአሰራር ሥርዓትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ በተለይም በሴቶች በሚመሩ ኢንተርፕራይዞች ከሥራዬ/one ILO, Siraye Programme) በመተባበር በመተግበር ላይ ያለው Women Leadership Development Intervention እና የሥራ አካባቢን ለሰራተኛ ምቹ በማድረግ የተገኙ ዉጤቶችንና ልምዶችን አዎንታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑን አቶ ዳንኤል አስረድተዋል ፡፡

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post