በሴቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እድገትን ያፋጥናል"

አዲስ አበባ የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሌበር ኦርጋይኔዜሽን ጋር በመተባበር በአምራች ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ በተለይም በሴቶች በሚመሩ ኢንተርፕራይዞች የሴቶች አመራር ልማት ፕሮግራም ለማሳደግ እና ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተጀመረው ፕሮግራም ውጤት እያመጣ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሴቶችና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ እየሩሳሌም ዳምጤ ገልፀዋል ።

ሴቶችን ወደ አመራርነት እንዲበቁ ለማድረግ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ለኢንተርፕራይዞች መሰጠቱን የገለፁት ስራ አስፈፃሚዋ በተለይም ለሴቶች የስራ አካባቢ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ እና የማምረት አቅም አጠቃቀምን ከማሳደግ አንፃር እንዲሁም ወደ ከፍተኛ አመራርነት የማብቃት ተግባራት ሰፊ ስራዎች በፕሮግራሙ መከናወናቸውን አስረድተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪዎች ዉስጥ በተለይም በሴቶች በሚመሩ ኢንተርፕራይዞች የተገኙ ዉጤቶችንና ልምዶችን አዎንታዊ ተፅዕኖ የፈጠሩ ናቸው ያሉት ወ/ሮ እየሩሳሌም በሴቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ በዘርፋ ላይ እድገትን እንደማያመጣ ገልፀዋል ።

የሥራ አካባቢን ለሰራተኛ ምቹ ያደረጉ ኢንተርፕራይዞች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የምስጋና ሰርተፍኬት መስጠቱን አስረድተዋል ።

ሰርተፍኬቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በተለይም ለሴቶች ምቹ የሥራ አካባቢ በመፈጠር በቀጥታ ለምርትና ምርታማነት ከፍተኛ አስተዋፆ ያለዉ በመሆኑ ለሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎች አርአያ ስለሚሆኑ የጀመሩትን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post