የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ መጤ አረም ፕሮጀክት አፈፃፀም ሂደት እየተገመገመ ነው

መጋቢት 03/2016 ዓ.ም (ኢሚ) በአየር ንብረት ለውጥ ፐርፎስማንስ ፕሮጀክት በፐሮሶፒስ ጁሊ ፍሎራ መጤ አረም (ወያኔ አረም) የተወረሩ የእርሻና የግጦሽ መሬቶችን በመመንጠር የመጤ አረሙን አማራጭ የኃይል ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግልና መሬቶችን መልሶ ለሰብል ምርት እንዲውሉ ማድረግ አላማ በማድረግ ወደ ስራ የገባው ፓይለት ፕሮጀክት የእስከ አሁን የስራ አፈፃፀሙ ደደይ ምርትና አገልግሎት በተባለ አማካሪ ድርጅት ዳሰሳዊ ጥናት ተዘጋጅቶ የሚመለከታቸው የፌደራል፣የክልልና ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የሙያ ማህበራትና ፕሮጀክቱን የሚደግፉ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ሪፖርቱ ቀርቦ እየተገመገመ ነው።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዳዊት አለሙ የፓይለት ፕሮጀከክቱን የስራ አፈፃፀም ጥናታዊ ሪፓርት ግምገማ ሲያስጀምሩ እንደገለፁት ሪፖርቱን በጥልቀት በመገምገም የፓይለት ፕሮጀክቱ አዋጭነትና ለአካባቢው ማህበረሰብ እያመጣ ያለውን አዎንታዊ ፋይዳ፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና ክፍተቶችን በመለየት ፕሮጀክቱን ሌሎች የግል ኩባንያዎች ወስደው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የፕሮጀክቱን የስራ አፈፃፀም ጥናታዊ ሪፓርት ያቀረቡት የደደይ ምርትና አገልግሎት አማካሪ ድርጅት ባልደረባ ዶክተር ጉታ ለገሰ በበኩላቸው ፓይለት ፕሮጀክቱ መልካም የሚባል አፈፃፀም ያለው በመሆኑ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በተግባራዊ ጥናት ያረጋገጡ መሆናቸውን በመግለፅ ፕሮጀክቱ ከሙከራ ትግበራ በመውጣት ወደ ሙሉ ትግበራ በመግባት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የኃይል አማራጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ የብዙኃኑን ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለበት ብለዋል።

በፓይለት ፕሮጀክቱ ጥናታዊ ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ የፕሮጀክቱን የስራ ሂደት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚያስችል ግብዓት እንደሚገኝ ይጠበቃል ።

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post