በአቶ መላኩ አለበል የተመራ የፌዴራል አመራሮች የሱፐርቪዥን ቡድን በአፋር ክልል የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጉብኝተዎል።

መጋቢት 11/2016ዓ.ም(ኢ.ሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የተመራ የፌዴራል አመራሮች የክትትልና ድጋፍ ቡድን በአፋር ክልል ምልከታ አድርገዎል።

ቡድኑ የክትትልና የድጋፍ ስራውን ከመጋቢት 06 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ አወል አርባና ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር ባካሄደው የጋራ ውይይት የጀመረ ሲሆን ባለፉት ጊዜያት በክልሉ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት እንቅስቃሴዎችን ምልከታ አድርጓል።

በተለይም የበጋ መስኖ ልማት እንቅስቃሴ፣ የሌማት ትሩፋት ፕሮግራሞች አፈፃፀም፣ የማንፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ እንዲሁም የትምህርት፣ ጤና እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን የሚመለከቱ አጠቃላይ የልማት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ምልከታ ተደርጎባቸዋል።

በተጨማሪም የስራ እድል ፈጠራን በሚመለከት የተከናወኑ ስራዎች በድጋፍ ቡድኑ የታዩ ሲሆን ወጣት ሴቶች በእደ ጥበብ ስራ፣ ወጣቶች በእርሻ የግብርና ስራ፣ በአሳ ልማት፣ በጨው ማምረት እና በሌሎችም ዘርፎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን በተካሄደው የመስክ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉ ተጠቅሷል።

ምንጭ ኢቢሲ

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post