የተቋምን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና ለማሻሻል የሚያስችል ስልጠና በካይዘን የልህቀት ማዕከል ተሰጠ

መጋቢት12/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) ስልጠናው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በካይዘን ልህቀት ማዕከል ለሰራተኞችና ለተገልጋዮች ምቹና ሳቢ የስራ ቦታ በመፍጠር የግብዓትና የጊዜ ብክነት በማስወገድ፣ወጪን በመቀነስ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን በማሳደግ ለአገልግሎት ሰጪውና ተቀባዩ የስራ አካባቢ ምቹ ማድረግ ዋና አለማ ያደረገ ነው፡፡

የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን ሙሀመድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰራተኞችን አቅም ከመገንባትና ምቹ የስራ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ስልጠናው የተዘጋጀው ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከካይዘን ልህቀት ማዕከል ጋር ተቀናጅቶ የተሰራ በመሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚዎች ተሳትፈዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post