በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር ያስፈልጋል (አቶ ሀሰን መሀመድ)

መጋቢት13/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ) በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር የሚረዳ የውይይት መድረክ ተካሄዷል፡፡

ህንድን ከኢትዮጵያ ጋር ያገናኘው የኬሚካል ገዥና ሻጮች የውይይት መድረክ ላይ የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን ሙሀመድ የተደረገው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል በትብብር ለሚሰሩ ስራዎች እና ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገት በሮችን የሚከፍት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አክለውም የህንድ ኬሚካል ኢንዱስትሪ እና በኢትዮጵያ ገበያ መካከል የንግድ አጋርነት መጎልበት ትልቅ እመርታ ይኖረዋልም ብለዋል፡፡

በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ የኬሚካል ዘርፍ ፍላጎት በህንድ የኬሚካል ምርቶች እና በህንድ ላኪዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለማስተካከል ዓላማ የያዘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ገበያዎችን ለማገናኘት እና የእርስ በርስ ግንኙነትን በመፍጠር ሽርክናዎችን በማጎልበት የሀገራቱን ገበያ ያሳድጋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቀጥታ ኢንቨስትመንት ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ ከሚሳታፉ ሀገራት መካከል ህንድ በሁለተኛ ደረጃ ትገኛለች፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post